ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ መንግስት በመፍጠር ቃላችንን በመተግበር የህዝባችንን ህይወት ለመለወጥ በላቀ ቁርጠኝነት እንሰራለን ፦አቶ በላይ ተሰማ
የብልጽግና ፓርቲ ምክርቤት አባል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት ምስረታ እና በገቢር ነበብ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ባላፉት አምስት ዓመታት አባሉን አመራሩንና ህዝቡን በማስተባበር በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መስክ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን እነዚህ አኩሪ ድሎች ያስመዘገበው የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጥበብ በመሻገርና ወደ ዕድል በመቀየር እንደሆነ በመግለጫቸው አብራርተዋል። በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ያስመዘገባቸው ድሎች ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ በአዲስ ኃላፊነትነና በአርበኝነት ስሜት እመርታ ለማስመዝገብ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል። ጠንካራ ፓርቲና መንግሥት በመገንባት የወል ሕልማችን ዳር እንዲደርስ የድርሻችንን በማበርከት የሀገራችንን ቅቡልነትና ከፍታ ከግብ እንዲደርስ በጉባኤው አቅጣጫ መቀመጡትን የገለጹት አቶ በላይ ለተግባራዊነቱም መላው አማራሩን፣ አባሉንና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ትግል ይደረጋል ብለዋል። የተጀመሩት የፓርቲያችን ጉዞ የሀገራችንን ሁለንተናዊ የፓለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ስብራቶች የሚጠግን ነው። በዚህም የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ ሀገራዊ ባህልን ከመሠረቱ እየቀየረ ወደ አዲስ ባህል የሚያሸጋግር ሁለተናዊ የብልጽግና ጉዞን የሚያሳልጥና መጻኢ ጊዜን ብሩህ ተስፋን የሚያላብስ እንደሆነ ገልጸዋል። የተጀመረውን የተቋማት ሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ነጻ ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት ግንባታ ስራዎችን በማስቀጠል ጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ለመገንባት ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የገለጹት አቶ በላይ በዚህም የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት ግንባታ በጽኑ መሰረት ላይ ለማኖር በብርቱ ትግል ለመከወን በጉባኤው አቅጣጫ መቀመጡን አብራርተዋል። በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በመቅረፍ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ፈጣንና ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማሳለጥ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የገለጹት ኃላፊው በመፍጠርና በመፍጠን አገልገይ ተኮር እሳቤን በመላበስ በቁርጠኝን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። የብሔራዊነት ገዥ ትርክት እንዲሠርጽና በሕዝቦች መካከል ትስስርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲፈጠር በጉባኤው አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ገዥ ትርክትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አመራሩና አባሉ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል ። የአመራሩን እና የአባላትን ብቃትና ጥራት በማሳደግ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ብልጽግና የሆኑ፣የፓርቲውን እሳቤዎች ፣ፕሮግራሞች እና ተልዕኮ በውጤታማነት ተተግብረው የህዝቡን ህይወት ለማሻገር እና የኢትዮጵያን ህልም እውን ለማድረግ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ በትጋት ይሰራል ብለዋል። በቀጣይ የብልጽግና ህብረትና የብልጽግና ቤተሰብ ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናችን በመወጣት የህዝቡን ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል። የፓርቲው የልማት አደረጃጀቶች በክልሉ ለሚከናወኑት ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት ያስቻለ መሆኑንም ገልጸዋል። በፓርቲው ሁለተኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ከግብ ለማድረስና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማሳለጥ የክልሉ ህዝቦች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

