በ90 ቀናት ውስጥ ሀሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ የክልሉን ከፍታ የሚያረጋግጥና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተግባራት በልዩ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ አቶ ፍቅሬ አማን
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በ90 ቀናት ውስጥ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትንና የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ከካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ እንዳሻው ከበደ ጋር የውል ስምምነት ፈጽመዋል። በውል ስምምነት ስነ ስርዓት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ እንደገለጹት በዘጠና ቀናት ውስጥ የብልጽግና እሳቤዎችን በላቀ ብቃት ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል። በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ ከምንም ጊዜ በላይ በልዩ ትጋትና የቁርጠኝነት እሳቤን ተላብሶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። በዚህም በዘጠና ቀን የታቀዱ የመቀነስ ግብ የዜሮ ግብ፣ የሁለት ድጅት ግብ፣ የአንድ ግብ ና የ100% ግቦችን በላቀ ብቃት ተግባራዊ ለማድረግ የውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል። በተለይም የክልሉን እምቅ አቅሞችና ዕድሎችን ወደ ተጨባጭ ሀብትነት ለመቀየር በመፍጠን፣ በመፍጠንና በዝላይ እሳቤን ተላብሶ የአመራር ለውጥ በማምጣትና የስራ ባህልን በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ዋነኛ ተግባር እንደሆነ አሳስበዋል። አመራሩ ከተለምዷዊ የስራ ባህል የተሻገረ አስተሳሰብን በመላበስ ኑሮ ውድነት ፣ሌብነት ፣መንደርተኝነትና ጠበቂነት መቀነስ እንደሚገባም አሳስበዋል። የአንድ ግቦች የሆኑትን አንድ የገጠር ኮሪደር በወረዳ፣ አንድ የምርት ማከማቻ በወረዳ፣ አንድ የቱሪስት መዳረሻ በዞን ፣አንድ የእንስሳት ጤና ማዕከል በአርብቶ አደር ዞን፣አንድ የመሶብ አገልግሎት ማዕከል በከተማ ፣ አንድ የሽያጭ ማዕከል በከተማ በመግንባት እነዚህንና ሌሎች ግቦችን ለማሳካት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መትጋት ይጠበቃል። ከግብ ስምምነት መካከል የኑሮ ውድነትን መቀነስ ሲሆን ለዚህም ምርትና ምርታማነትን መጨመር ወሳኝ ነው ያሉት ኃላፊው አንድም ሊላማ የሚችል መሬት ጾም ማደር የለበትም ብለዋል። ምርታማነትን ለማሻሻል በሚረዱ አሠራሮች ላይ የገለጹት ኩታ ገጠም እርሻ፣የምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አጠቃቀም ፣ ሜካናይዜሽን እርሻን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተረጂነት ዜሮ ማድረግ ይገባል ነው ። እንደ አቶ ፍቅሬ ገለጻ ተፈናቃይነት ፣ኮንትሮ ባንድ ፣ሽፍታና ሌብነትን ዜሮ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መትጋት ይጠይቃል ብለዋል። የፋይዳ መታወቂያ፣አምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፣ኮሪደር ልማት ፣ የገበታ ለትውልድ ፣የምርጫ ምቹነት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎንምን ውጤታማ ቅንጂታዊ አንድነትን በማሳለጥ የተቀመጡ ግቦችን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል። አመራሩ የባሀል ለውጥ በማምጣት ፣የአገልጋይ ተኮር እሳቤን በመላበስ ህብረተሰቡን ማገልገል ይጠበቃል ያሉት አቶ ፍቅሬ የስራ ምቹነትን የሚፈጥሩ አሰራሮችን በመተግበር ተቋማዊ ለውጥ ለመፍጠር ጠንክሮ መስራትን ጊዜው ይጠይቃል ነው ያሉት። የሌማት ትሩፋትን ማስፋትና ማጠናከር፣ኩታ ገጠም እርሻ፣ የበጋ እርሻ ፣ማዕድንና ሌሎች የሁለት ዲጂት ግቦችን ለማሳለጥ በትጋት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

