በ90 ቀናት ውስጥ ሀሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ የክልሉን ከፍታ የሚያረጋግጥና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተግባራት በልዩ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ አቶ ፍቅሬ አማን
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በ90 ቀናት ውስጥ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትንና የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ከካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ እንዳሻው ከበደ ጋር የውል ስምምነት ፈጽመዋል። በውል ስምምነት ስነ ስርዓት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ እንደገለጹት በዘጠና ቀናት ውስጥ የብልጽግና እሳቤዎችን በላቀ ብቃት ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል…

