dawuro zone

ዳዉሮ ዞን እስከ 2010 ዓ/ም ድረስ አምስት ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር የነበሩት ሲሆን ከጥቅምት 2011ዓ/ም ጀምሮ አምስት ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ተጨምሮ አስር ወረዳ እና ሁለት ከተማ አስተዳደርአሉት::
ዳዉሮ “የሚለዉ ስም የብሔሩና የዞኑ መጠሪያ ሲሆን እንደ ብሔሩ ትርጉም ጀግና፣ጎበዝ፣ታታሪ፣ ደፋርና ኩሩ የሚል ስያሜ እንዳለ ይገለጻል. (ተረፈ ገብሬና ሌሎች 1987 ዓ/ም በወንድሙ ልማ እና ሙሉጌታ ዛብህ 2003ዓ/ም እንደተጠቀሱትበቋንቱ ቤተሰብ መሠረት ዳዉሮ ” አሟዊ ህዝቦች ” ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል፡ቋንቋዉ ዳውረኛ ስሆን በመላዉ ዞን እና አጎራባች አከባቢዎች ይነገራል፡፡ የዞኑ ሕዝብ ብዛት በማእከላዊ እስታትከስ ጥሮጀከሽን መሰረት ከ850 ሺህ በላይ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
የዳዉሮ ፖለቲካዊ አስ/ር አደረጃጀትን ስንመለከት በግምት ከ12ኛ ክ/ዘመን በፊት ጀምሮ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር ጠንካራ የአስተዳደር መዋቅር የገነባ ሀገር(STATE/ KINGDOME) ነበር:: ከ16ኛዉ አስከ 19ኛ ክ/ዘ ፖለቲካዊ መዋቅር በማሻሻል ቤተ መንግስትን ከአሁኑ ዲሳ ወረዳ ኩይሊ ቀበሌ ወደ ደጋዉ ከፍታ ቦታ ሎማ ወረዳ ኮይሻ ካቲ ጋ ዋ ላይ በማቋቋም 14 የሚሆኑ ነገስታት በካዉካ ሥርወ-መንግስት አስተዳድረዋል፡፡ ዳውሮ በዳግማዊ ሚኒሊክ ወረራ በ1885ዓ/ም የኢ/ያ ማእከላዊ መንግስት አካል ሆኗል፡፡


የዳውሮ ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀት ስንመለከት በዞኑ ዉስጥ ከጥንት ጀምሮ የእርሻ ስራ፤ብረታብረት ስራ፤ማእድናት ማንጠር፤ሸማኔ ስራ ፤የሸክላ ስራ፤ የቆዳ ስራ፤የአናጺነት ስራ፤አደን ማደን፤ ንግድ በስፋት ይከናወናል፡፡ ከሙያቸው አንፃር በሳይንሳዊ እይታ የዳውሮ ጥንታዊነት ከሚያረጋግጡት ተግባር አንዱ ደንቻዎች በዋናነት የሚተዳደሩበት በቆዳ ሥራ ነው፡፡ ቆዳን በድንጋይ በመፋት (ማንቻላ) ቴከኖሎጂ የጥንት ናይሎቲከ ሥልጣኔ ቴክኖሎጂ ሆኖ ከዓለም የጠፋው ነገር ግን በዳውሮ እስከ ዛሬ በተግባር መታየቱ ጥንታዊ መሠረት እንዳለ የኢንትሮፓሎጂ እና የሶሽዮሎጂ ተመርማሪዎች ይጠቁማሉ ::

(ከሉላፓንክሬስትና ገብሬይንትስ2007)በአለም በርዝመት ተወዳዳሪ የሌለዉ የእስትንፋስ ሙዝቃ መሳሪያ ድንካ የዳዉሮ ብሄር ከሚታወቅበት አንዱ ስሆን ለደስታም ሆነ ለሀዘን ዘዉትር ይጠቀማሉ፡፡
ዳዉሮ ለግብርና ስራ ምቹ ከሚባሉ አከባቢዎች አንዱ ስሆን በቆሎ፤አተር ፤ጤፍ ፤ገብስ ፤ማሽላ ፤ስንዴ በብዛት ይመረታል፡:: ፣በካጪ በዲሳ፣በገና እና ሌሎች ወሪዳዎች ሰፊ መሬት ወስደው ባለሀብቶች በግብርና ተሰማርተው ይገኛሉ ::

ዞኑ በአሁኑ ሰዓት የድንጋይ ከሰልን ለማዕከላዊ መንግስት በከፍተኛ ሁኔት ከሚያቀርቡ አከባቢዎች አንዱ ነው ::በገበታ ለሀገር የተገነባው የሀላላ ከልስተር የመዝነኛ ሎጂ ለቱርዝም እንቅስቃሴ ምቼ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል :፤በአንድ ረድፍ 175 ኪ.ሜትር እና በአጠቃላይ ርዝመት በሳባት ረድፍ 1225 ኪ.ሜትር የሚሸፍን ከ2.5 እስከ 5 ሜትር ስፋት ከ2.5 እስከ 3.8 ሜትር በላይ ከፍታ ያለው ከ200 አመት በላይ ለግንባታ የፈጀው የንጉስ ሀላላ የጦር መከለካያ ግንብ ሌላኛው የዘኑ ትልቁ ቅርስ ነው::

በተጨማሪም በሎማ ኮይሻ ያለዉ የንግሱ ዋናው በቴ- መንግሥት፣ በድንጋይ ተበርብሮዉ የተዘጋጀ የቤተ መገለገያ ዕቃዎች፣ በቶሜ ያለዉ አንጋላቲ ጋቤ መደብ፣በኮንታና በዳዉሮ ዞኖች መካከል ያለዉ የጨበራ ጩርሪ ብሔራዊ ፓርክና ለእይታ ሳቢ የሆኑ የዱር አራዊቶች ፣በጊቤ- 3 ኤለክትሪክ ኃይል ማመንጫ ምከንያት የተፈጠረዉ ሰዉ ሰራሽ ሀይቅ ተጨማሪ ለአከባቢ ኢንቨስትመንትና ቱርዝም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከታል፡፡
በዞኑ ዉስጥ 429 መደበኛ ትም/ቤቶች ያሉት ስሆን ከ2 መቶ 50 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የታርሜ ጠቅላላ ሆስጥታል፣ የቶሜና የገሳ ጫረ መጀመሪያ ደረጃ ሆስጥታል በዞኑ የጤና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሆስፕታሎች ስሆን የዋካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፕታልም ይገኝበታል ።