የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት ሁለተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጠና በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጠና መካሄድ ጀምሯል ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ የገጠር የመዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ፣የኢንዱስትሪ ዘርፍ ፣የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል። በስልጠናው መርሃ ግብር የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በአመራሩ መካከል የአስተሳሰብ አንድነትን መፍጠር ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል። የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴቶችን ለማጠናከር እንዲሁም የውሰጠ ፓርቲ አንድነትን ይበልጥ ለማጎልበት ስልጠናው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። ስልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም ከመገንባት ባሻገር የመፈጸም እና የማስፈጸም ብቃት ያላቸው አመራሮችን ለማፍራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ከስልጠናው በተጓዳኝ ለልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመቀመር የተለያዩ የልማት ስራዎች የመስክ ጉብኝት የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል። ለተከታታይ 9 ቀናት በሚቆየው ስልጠና 677 ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ/ከተማ አስተዳደር ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *