የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮን በብቃት ማስፈጸምና መፈጸም የሚችል አመራር በተገቢው ማጥራትና መልሶ የማደራጀት ስራዎች ተሰርተዋል ፦ አቶ ፍቅሬ አማን
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ክልላዊ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉት አመራሮች የግምገማና የምዘና መድረክ በጥብቅ ዲስፕሊን በመምራት አመራሩን በተገቢው መመዘን መቻሉን አስታውሰዋል። ግምገማው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የ2018 የፓርቲና የመንግስት ድርብና ድርብርብ ተልዕኳዎችን ማስፈጸምና መፈጸም የሚችሉ አመራሮችን ለመፍጠር ከወትሮው በተለየ መልኩ የክልሉን ነበራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ጥልቀት ያለው ሰነድ በማዘጋጀት ችግሮችንና ጥንካሬዎችን በማሳየት የአመራር ግምገማና ምዘና መካሄዱን ተናግረዋል። ይህንን ግምገማ መነሻ በማድረግ ተልዕኮዎችን በቁርጠኝነት መፈጸምና ማስፈጸም የሚችል የአመራር ስምሪት በአዲስ መልክ ማዋቅር መቻሉን አቶ ፍቅሬ አብራርተዋል። በዚህም በክልል ማዕከል በተደረገው ግምገማ ወንድ 10 ሴት 5 በድምሩ 15 አመራሮች ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነተቻው የተነሱ ሲሆን በሽግሽግ ወንድ 18 ሴት 6 በድምሩ 24፣ በአዲስ መልክ ወደ ክልል አመራርነት የተቀላቀሉ ወንድ 18 ሴት 2 ድምር 20 በአጠቃላይ 59 አመራር ከኃላፊነት የማንሳት፣ የማሸጋሸግና በአዲስ መልክ ወደ አመራር ፑል የመሳብ ስራዎች መሰራቱን አብራርተዋል። የአመራር ግምገማው ውጤታማነትን፣ስነ ምግባርንና ዝግጁነትን መሠረት በማድረግ በጥልቀት የተገመመገመ መሆኑን ጠቁመዋል። አመራሩን ከውጤታማነት አንጻር፣ የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮዎችን በተገቢው ከመፈጸም ከማስፈጸም አንጻር፣ ህዝቡ በብልጽግና ፓርቲ እንዲፈቱለት የሚፈልገው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር ግምገማው በጥልቀት መገምገሙን ጠቁመዋል። ፓርቲያችን አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚመጥንና ቀጣይ ተልዕኮን በብቃት ለመፈፀም የሚያስችል ጠንካራ አመራርና ለመፍጠር የተረገ ግምገማ መሆኑን ገልጸዋል። የተመደቡ አመራሮች መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በአዲስ ኃላፊነትና ተነሳሽነት፣ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ተልዕኮዎችን በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል።

