የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ግንባታን ለማፋጠን ወጣቱ አይተኬ ሚናውን ሊወጣ ይገባል፦ አቶ ነጋ አበራ
የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ግንባታን በማፋጠን ሂደት ውስጥ ወጣቱ አይተኬ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ አሳሰቡ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለወጣቶች እየሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። በስልጠናው ከወጣቶቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት ብሔራዊ ገዥ ትርክት መሰረት እንዲይዝና እንዲጸና ወጣቱ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ የተቀናጀ ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። ወጣቶች በሀገር እና ሀገረ-መንግስት ግንባታ እንዲሁም በሠላም እሴት ግንባታ ላይ እያበረከተ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል ለሁለንተናዊ ብልጽግና ስኬት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል። ብልጽግና ባለፉት ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን በመጠገን ለትውልድ ምንዳን ለማውረስ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም ወጣቶች የብልጽግና እሳቤዎች በሆኑት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ወንድማማችነትና አህትማማችነትን እሴቶችን በማዳበር የጋራ ብልጽግናችን ለማረጋገጥ በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ይጠበቃል ብለዋሌ። የተጀመሩ ሀገራዊና ክልላዊ ኢኒሼቲቦችኝ ዘላቂና ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያለው ወጣት የድርሻውን እንዲወጣ አስገንዝበዋል ።

