ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የህዝብ ለህዝብ ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንዲሰሩ ተጠየቀ።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር፣ ማስተማር ስራ እንዲቀጥል በማድረግ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ያለመ የውይይት መድረክ ከክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ ፣ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ ፣እንዲሁም ከክልሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮችና የባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምምክር መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱ፥ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነባራዊ ሁኔታን የሚዳስስ ሪፖርት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የኾነው ሪፎርም አውንታዊ ለውጥ እያመጣ መኾኑን የገለጹት የክልሉ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ የሚገጥሙ ችግሮችን በየጊዜው በጠንካራ አደረጃጀት እየገመገሙ መፍታት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የብዝሀ ሀሳብ እና እውቀት ምንጭ ናቸው ያሉ አቶ ፍቅር በጥናትና ምርምር ስራዎቻቸው እንዲሁም በማኅበረሰብ አግልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮችን ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የጋራ ፎረም መመሥረት እንዳለበትም አቶ ፍቅሬ ጠቁመዋል።

የትምህርት ጥራት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረትም ዩኒቨርስቲዎች የጀመሩትን የማበረታቻ ተግባራት መጠናከር እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፍቅሬ፣

የትምህርተት ጥራትን በመሠረታዊነት ማረጋገጥ በሚቻልበት አግባብ ላይ ዩኒቨርስቲዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በቅንጅት እንዲሰሩም በአጽንኦት ጠይቀዋል።

ዩኒቨርስቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በተገቢው እንዲወጡ ጠንካራ አደረጃጀት የጎላ ፋይዳ እንዳለውና ይህም ከተቋማዊ አሰራር ጋር በማይጣረስ መልኩ መኾን እንዳለበትም አቶ ፍቅሬ አስገንዝበዋል።

ሠላማዊ የመማር ማስተማር ተግባሩ በዩኒቨርስቲዎች እንዲቀጥል ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ ለዚህም ከአካባቢ መንግሥት ጋር በትብብር መንፈስ መስራት ወሳኝ እንደሆ ጠቁመዋል።

በዩኒቨርስቲዎች ለሀገር የሚተርፍ ሀሳብና እውቀት ያለ በመኾኑ ተቋማቱ ተልዕኮቻቸውን ከማኅብረተሰቡ የልማት ፍላጎት ጋር በማጣጣም ለአከባቢ ልማት እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብቱም አቶ ነገ አሳስበዋል።

በመድረኩ የተገኙ የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው፥ በዩኒቨርስቲዎቻቸው ውስጥ አሉ ስላሏቸው ችግሮች በዝርዝር አንስተው የክልሉ መንግሥት በቅርበት እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል።

በቀጣይ የማኅበረሰቡን ኑሮ በዘላቂነት በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፥ በተቋማቱ የተጀመረው የለውጥ ትግበራ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ የክልሉ መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል።

የተቋማትን ተልዕኮ በላቀ መልኩ ለመፈጸም ከክልሉ መንግሥት ጋር ተቀናጅተው መስራት ወሳኝ መኾኑን የገለጹት የመድረኩ ተሳታፊዎቹ፥ በወሳኝ የጋራ ጉዳዮች ቀጣይነት ያለው የጋራ መድረክ በየጊዜው መፈጠር እንዳለበም አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *