‎የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ግንባታን ለማፋጠን ወጣቱ አይተኬ ሚናውን ሊወጣ ይገባል፦ አቶ ነጋ አበራ

የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ግንባታን በማፋጠን ሂደት ውስጥ ወጣቱ አይተኬ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ አሳሰቡ ‎ ‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለወጣቶች እየሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ‎ በስልጠናው ከወጣቶቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት ብሔራዊ ገዥ ትርክት መሰረት እንዲይዝና እንዲጸና ወጣቱ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ የተቀናጀ ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። ‎ወጣቶች በሀገር እና ሀገረ-መንግስት ግንባታ እንዲሁም በሠላም እሴት ግንባታ ላይ እያበረከተ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል ለሁለንተናዊ ብልጽግና ስኬት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል። ‎ ‎ብልጽግና ባለፉት ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን በመጠገን ለትውልድ ምንዳን ለማውረስ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ‎ ‎በዚህም ወጣቶች የብልጽግና እሳቤዎች በሆኑት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ወንድማማችነትና አህትማማችነትን እሴቶችን በማዳበር የጋራ ብልጽግናችን ለማረጋገጥ በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ይጠበቃል ብለዋሌ። ‎ ‎ የተጀመሩ ሀገራዊና ክልላዊ ኢኒሼቲቦችኝ ዘላቂና ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያለው ወጣት የድርሻውን እንዲወጣ አስገንዝበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *