የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ልዑክ የወጣት ለወጣት ግንኙነት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን እያካሄደ ነው
የፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በካፋ ዞን፣ቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በካፋ ዞን፣ቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቦንጋ ማዕከል እየተሰሩ ያሉ የዘር ዝግጅት እንዲሁም በክልሉ ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የቦንጋ ምርምር ማዕከል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
እንግዶቹ ፥ የካፋ የነገሥታት መናገሻ ስፍራ በኾነው ‘ቦንጊ ሸምቤቶ’ የሚገኘውን የካፋ ባህል ማዕከል ላይም በመገኘት የተለያዩ ቅርሶች ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንጨምሮ ሌሎች የክልል ፣የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

